
ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው ወንድማችንን እንታደገው
Donation protected
""50 ሎሚ ላንድ ሰዉ ሸክሙ ነዉ ለ 50 ሰዉ ግን ጌጡ ነዉ "" "ሁሉም ቢተባበር የት እንደርስ ነበር" ወገኖቸ እንዴት ናችሁ :ዶ/ር መስከረም አበባው ከበደ እባላለሁ በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ሀኪም ነኝ።ባለቤቴ ዶ/ር ንጉስ ሸጋው አውለው ይባላል ከባህርደር 43 km ርቀት ላይ በምትገኘው አዴት የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል በአጠቃላይ ሀኪምነት እየሰራ ነበር።ሁለታችንም የጥቁር አንበሳ የ 2011 ተመራቂወች ነበርን።ከንጉስ ጋር ለ አመታት ያህል በጒደኝነት አሳልፍን ከወራቶች በፊት ነበር የተጋባነው።ስለ ባለቤቴ ንጉስ ሁሉ ነገሬ በየ ብጠራው እመርጣለሁ።ሆኖም ባደረበት ህመም ምክንያት ምርመራ አድርጎ የደም ካንሰር/acute meloid leukemia እንዳለበት ባለፈው ሳምንት ተነግሮታል።አሁን ላይ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገለት ይገኛል።በዘርፉ የሚመለከታቸውን የህክምና ባለሙያወች አናግሬ ነበር። የደም ህዋስ ግንድ ንቅለ ተከላ/hematopoietic stem cell transplant ማድረግ እንዳለበት እና ይህ ህክምና ደግሞ እኛ ሀገር መስጠት እንደማይቻል ውጭ ሂዶ መታከም እንዳለበት ተነግሮኛል።ይህ ህክምና ከፍተኛ ወጭ የሚጠይቅ በመሆኑ በእኝ አቅም ማሳከም አልቻልንም።እየተባባሰ የመጣው የ ኮሮና ቫይረስ ደግሞ ነገሮችን ለማስፈፀም በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሁኖብናል። ውድ ኢትዮጽያውያን የባለቤቴን የ ዶ/ር ንጉስን ህይወት ለመታድግ በሀሳብ በገንዘብ እጃችሁን ትዘረጉልን ዘንድ በፈጣሪ ስም እጠይቃለሁ።በሽታው ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ ጊዜው እየተራዘመ በሄደ ቁጥር የመዳን ተስፋው እየጨለመ ስለሚሄድ እእባካችሁ በፍጥነት ህክምና እንዲያገኝ የቻላችሁትን አግዙኝ።ንጉስ ሂወቴ ሁሉ ነገሬ ነው።አባቴ በቂ ህክምና ባለማግኛቱ ገና የ13 አመት ልጅ እየለሁ ነበር በሞት የተለየኝ። ንጉስ ህክምና ማግኘት ካልቻለ በቅርቡ ልክ እንደ አባቴ ሁሉነገሬን ባለቤቴን አጣዋለሁ። ሀገራችንም ብዙ መስራት የሚችል ልጅ የነበረ ሰው ታጣለች።እባካችሁ እርዱን መርዳት ለምትፈልጉ የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000323020349 ዶ/ር ንጉሱ ሸጋው እና ዶ/ር መስከረም አበባው ስልክ ቁጥር 0923005854 ሰለረዳችሁን እናመሰግናለን ቢኒያም እንደተረጎመዉ በተጨማሪም በቴሌግራም በተከፈተ ግሩፕ በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን https://t.me/suportmeski ከኛ ጋር በቴለግራም ሃሳብ ለመለዋወጥ ከፈለጉ በዉስ መስመር ያዉሩን "" ሠዉን ለመርዳት ሠዉ መሆን በቂ ነዉ"" ደግ ደጉን እናስብ መልካሙን እናድርግ
Organizer
Betelhem Dagnachew
Organizer
Geneva, GE