
ለወሎ ህዝብ ከርሀብ እንዲድን የድርሻችንን እንርዳ
Donation protected
ከኢትየጵያ ፓለቲካዊ ርምጃ
መድረክ (EPAC) - FORUM
የተሰጠ መግለጫ መስከረም3ቀን 1914 (September13-2021)
በሰሜን ወሎ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወጎኖቻችን ላይ የደረሰውን እጅግ እሳዛኝ ጥቃት ና ሰው ሰራሽ ርሀብ መሰረት በማድረግ
የፎረሙ ኣስተዳደር በዛሬው እለት ተሰብስቦ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ኣካሂዱኣል ::በውይይቱም ማጠቃለሊያም የጉዳዩን ኣሳሳቢነት ከግንዛቤ በማስገባት በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ : ርሀብና እርዛት ብሎም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወጎኖቻችን ህይወት ለማደን ኣስቸኩኣይ ድጋፍና እርዳታ ለማሰባሰብ የሚረዳ ወገናዊ ጥሪ በአስቸኩኣይ ለማድረግ ወስነናል::
በወያኔ ወራሪ ሀይሎች ቤት ንብረቱ ተዘርፎ የተረፈውም ወድሞበታል:: የሰሜን ወሎ ህዝብ ህይወቱን ለማትረፍ በእግሩ ከ አላማጣ: ከቆቦ: ከዋጃ: ከወልድያ: ከላስታ: ከ የጁ ዙርያ: ከመርሳ: ከውጫሌ: ከ እምባሰል: ከወረባቦ: በዚህ ሰሞን ደግሞ ከ ደላንታ: ተሰዶ በ ደሴ አካባቢ ተጠግቶ ይገኞል :: ምንም የመንግስት እርዳታ ሳይደረግለት የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ከራሳቸው የእለት ምግብ በማካፈል ህይወታቸውን ማዳን ቢችሉም ችግሩ ከ ደሴ ነዋሪዎች ኣቅም በላይ በመድረሱ እልቂት ማስከተል ጀምሩአል ::
ስለዚህም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ : ብሎም ስለ ሰው ልጅ ሰብአዊ የመኖር መብት የምትሙአገቱ ና ለወገን ደራሽ የሆናችሁ የሰሜን ወሎ ህዝብ ከእልቂት ለማዳን ይተቻላችሁን የእርዳታ እጃችሁን ዘርጉ ::
የኛ ጥሪም የድርሻችንን እናድርግ ለወሎ ህዝብ እንድረስለት ነው ::
ይህንንም በመንግስት የተደበቀ እልቂት ለ ኢትዮጵያኖች ና ለ ኣለም ህብረተሰብ እንዲያውቁት እናድርግ ! ለ ተራቡት እንርዳ ድምፅም እንሁናቸው !
እርዳታ ለምታደርጉ ጥያቄ ካላችሁ
በ [phone redacted] መደወል ትችላላችሁ
እርዳታውን የሚቀበለንን ለህዝባችን በፍጥነት ሊያደርስ ከሚችሉ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር ላይ ነን :: እርዳታችሁን የሚቀበለውን ድርጅት በይፋ እናስታውቃለን ::
ከ ኣክብሮት ምስጋና ጋር !
ሀይሌ ተፈራ
የ ፎረሙ ሰብሳቢ
Co-organizers (2)
Haile Tefera
Organizer
Sugar Land, TX
Legesse Gashaw
Co-organizer