
የመንበረ መንግሥት (ግቢ) ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን እድሳት ገቢ ማሰባሰቢያ።
Donation protected
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
“እነርሱም ይጠግኑና ያድሱ ዘንድ፥ የእግዚአብሔርን ቤት ለሚሠሩ ሠራተኞች ሰጡ።”— 2 ዜና 34፥10
የጣሊያን ጦር አገርን በወረረ ጊዜ ንጉሥ አፄ ምኒልክ ድንበር ለማስከበር ፣ለነጻነት ሊዋጉ ወደ አድዋ ለመዝመት ዝግጅት ላይ ሳሉ
ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ጂባትና ሜጫ አውራጃ ዱላ ከተባለ ቦታ አስመጥተው ከቤተመንግስታቸው አጠገብ ባለችው ስዕል ቤት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ላስቀመጡት ታቦተ ቅዱስ ገበርኤል ስዕሰትን ተሳሉ
አገሬን በጠላት ከተቃጣባት ጥቃት ከፈጣሪህ አማልደህ ድል እናደርግ ዘንድ አርዳን ጠላትን ድል አድርጌ ስመለስ ቤተ መቅደስህን አንጻለሁ ብለው
ከአድዋ ጦርነት በኋላም ኢትዮጵያውያን በወራሪው የጣሊያን ጦር ላይ ድል ተጎናጽፈው ፣ድንበር አስከብረው ፣ወራሪውን ጠላት አሳፍረው ሲመለሱ፤ ዳግማዊ ንጉሥ አፄ ምኒልከ በገቡት ስዕለት መሠረት
ይህንን ታላቅ እና ጥንታዊ ፤ የተዋበ የስነ ህንጻ ንድፍ ያለው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ሀገር ባለሙያዎችን ጭምር በማስመጣት በ1889 ዓ.ም አሳነጹ፡፥
ከተሰራ 126 ዓመታትን አገልግሎት በመስጠት ያስቆጠረው ታላቁ እና ጥንታዊው የመንበረ መንግሥት (ግቢ) ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ህንጻ ቤተክርስቲያን በእድሜ ብዛት በደረሰበት ጉዳት ምክንያት እድሳት እንደሚያስፈልገው በባለሙያ ተረገግጦ እድሳቱ ተጀምሯል፣ በመሆኑም
የአብሳሪውን መልአክ ቅዱስ ገብርኤልን ጥሪ ተቀብላችሁ ይህንን የበረከት ስራ ለመፈጸም እገዛ እንዲያደርጉ በችግርዎ ጊዜ ፈጣን ምላሽ በሚሰጥ በሊቀ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፤
የመንበረ መንግስት (ግቢ) ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ህንጸ ቤተክርስቲያን እድሳት ኮሚቴ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Organizer
Hiwot Taddesse
Organizer
Alexandria, VA