Alemgena Bethel Kale Heywet Church Building
Donation protected
በጌታ ለተወደዳች ሁና ለተከበራች ሁ ቅዱሳን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ!
የዓለም ገና ቤተል አጥቢያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ከዛሬ ሰባት ዓመታት በፊት ምንም ወንጌል ባልደረሰበት ቆርኬ በሚባል መንደር በአንድ ግለሰብ ቤት የተጀመረች ስትትሆን የጌታ ቃል እያሸነፈና እየበረታ በርካታዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ተጨምረው ባሁኑ ሰዓት በሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናን እግዚአብሔርን እያመለኩ ይገኙባታል።
ነፍሳት በጌታ አምነው እየዳኑ ከጨለማ ግዛት መላቀቃቸውን ያየ ጠላት ምዕመናንንም ሆነ መሪዎቻቸውን ማሳደድ፣ ማሳሰርና አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ሲያደርስ የነበረ ቢሆንም በጌታ አሸናፊነት ሠፊ መሬት ከመንግሥት አግኝታ ለማምለኪያ አዳራሽ፣ ለልጆችና ወጣቶች አገልግሎት፣ ለአዳዲስ ነፍሳት ማስተማሪያ ሥፍራ፣ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ማስተማሪያና ለሌሎችም ግልጋሎቶች የሚውል አዳራሽ እየሠራች ነው።
ጊዜያዊ ዳስ ውስጥ ሲያመልኩ የነበረ ቢሆንም አሁን ከመጥበቡም በላይ በላያቸው ላይ ሊወድቅ መድረሱን ከግምት በማስገባት ቤተ ክርስቲያኒቱ የግንባታ ሥራ ለመጀመር ተገድዳለች። ምዕመኖቿ የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ የሚገኙ ቢሆንም ካለው ወቅታዊ ፈተና ጋር ተዳምሮ ከአቅማቸው በላይ ሆኖ ስለተገኘ የሌሎች ወገኖችን ድጋፍ መጠየቅ አስፈልጓታል።
እኔ ወንድማችሁ ወርቅነህ ዳዊት ይህችን ቤተ ክርስቲያን ካስጀመሯት ወንድሞችና እህቶች መካከል ስለነበርኩ በታላቅ ስደት ፈታኝ በሆነ አካባቢ ወንጌል በማስፋፋት የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን የዚህን ኃላፊነት እንድወስድና አካውንቱን ከፍቼ ጥያቄያቸውን ወደናንተ እንዳቀርብ አደራ ተቀብያለሁ።
ተጨማሪ መረጃ ለምትፈልጉ በፌስ ቡክ ገጼ ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች መግለጫ ተለጥፎላችኋል። ጌታ አብዝቶ ይባርካች ሁ።

Organizer
Workneh Koyra
Organizer
Louisville, KY