ALEN! Amhara-Lives-Matter Emergency Fund
አለን! ለአማራ ህልውና አስቸኳይ ድጋፍ ዘመቻ
አለን!
ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩ በመላው አለም የሚገኙ 24 የአማራ ማህበራት ጥምረት - እየተካሄደ ያለውን የህልውና ትግል ያለአንዳች መንግስታዊ ጣልቃገብነት በሌለው ወይም መንግስታዊ የገንዘብ የማሰባሰቢያ ቋት ጋር ባልተገናኘ ሁኔታ - ይልቁንም እታች ምድር ላይ ወርደው የጋራ ህልውናችንን ለማስጠበቅ እየተጉ ያሉትን ተጎጂ ወገናችንን በተለይም ሳይወዱ በግድ ግብርናቸውን ጥለው ምትክ የለሽ ህይወታቸውን እየሰጡ ላሉ ገበሬዎች እና ቤተሰቦቻቸው የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ (በስንቅ፣ በመድሃኒትና በሌሎች ለህይወት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች) ለመርዳት አለን! ዓለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ሕብረት ይህንን ፍጹም እና ነጻ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀግብር አዘጋጅቷል፡፡
በዚህ ኢትዮጵያን ፈታኝ በሆነ ወቅት ላይ መላው ወገናችን በአንድነትና "ለወገን ደራሽ ወገን ነው" የሚለውን ብሂል በማጤን የአለኝታነት ድጋፋችንን በገንዘብ፣ በእውቀት፣ በጉልበት፣ በመረጃ እና በሞራል የመርዳት ታሪካዊ ግዴታ አለብን:: ስለሆነም እያንዳንዳችን በምንሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ይህንን ግዴታ እንድንወጣ ለወገናዊ ጥሪ አለን! ይሉ ዘንድ እድሉ ተመቻችቶሎዎታል፡፡
የአለን! ዓለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ጥምረት አባል ማህበራት፥
1. የአማራ ኮሚኒቲ በዩናይትድ ኪንግደም
2. የአማራ ማህበር በኦስትሪያ
3. ሞገድ የአማራ ማህበር
4. የአማራ ማህበር በጀርመን
5. የአማራ ወጣቶች ማህበር በኢትዮጵያ
8. የአማራ ማህበር በሆላንድ
9. የእራያ-አማራ አፌር
10. አማራ ማህበራዊ መገናኛ መድረክ
11. የአብን ድጋፍ ሰጪ በጀርመን
12. የአማራ ማህበር በኖርዌይ
13. የአብን ድጋፍ ሰጪ በሆላንድ
14. የሞረሽ ወገኔ አማራ ድርጅት
15. የፋኖ አማራ ድጋፍ ሰጭ ማህበር በእስራኤል
16. የአማራ ወጣቶች ማህበር በዌስተርን አውስትራሊያ
17. የፋኖ አማራ ድጋፍ ሰጭ በካናዳ
18. የአርበኞች ግንባር ታጋዮች በጎ አድራጎት ማህበር በአማራ ክልል
19. የአማራ ማህበር በሲውዘርላንድ
20. አማራ ሚዲያ ማዕከል አለም አቀፍ
21. የሀገራዊ ምክክር አደባባይ
22. የአማራ ማህበር በስዊድን
23. የአማራ ማህበር በፈረንሳይ
24. የአማራ ማህበር በኒውዝላንድ
You can make a difference by donating today on behalf of ALEN! to support the on-going struggle of Amharas for their survival.
ALEN!, a worldwide coalition of Amhara associations, is proud to stand with Moresh Wegenie Amhara Organization (MWAO), in facilitating on the ground support for the Amharas' life-and-death struggle for their survival and human-rights; doing so without any Ethiopian government intervention / mobilization. An impactful and trustworthy support channel is established as exhibited in ALEN!'s recent track records.
At a time when our Amhara Compatriots are fighting by putting their irreplaceable life on the line, all Ethiopians and particularly Amaharas worldwide have a historic obligation to provide support with finance, knowledge, energy, information, morale and prayer. Therefore, we implore for your goodness to fulfill this obligation with your financial support.
Please note that Moresh advocates for human rights of Amaras. Particularly Moresh works to educate / inform the Amara about its rich history and heritage that fuse its identifying assets and Ethiopian-ness. Moresh has the goal of helping the Amara to organize itself and ensure its opportunity for pursuit of happiness and to live in peace.