Main fundraiser photo

Support Asfaw Meshesha’s Challenging Journey

Donation protected
Support Asfaw Meshesha’s Challenging Journey
My name is Samson (Japi) Asfaw Meshesha, the son of Asfaw Meshesha, reaching out to you in a time of immense need. In October 2023, my father suffered a stroke while diligently carrying out his duties. Since then, he has been undergoing intensive care at the Axon Stroke and Spine Center and later continued his treatment at the George Washington University Hospital in Washington, DC.
This journey has been marked by both challenges and moments of grace. EBS television played a crucial role in covering his full medical expenses during the medical treatment. Moreover, EBS covered his travel accompanied by a nurse to the US. Upon his arrival in the United States, EBS generously supported me and my father and covered various expenses without hesitation. I am proud to say he is part of the EBS family, and their unwavering support has been a source of solace for our family.
During his hospital stay in Ethiopia, his EBS colleagues and friends have been by his side, taking turns to provide love and comfort. We extend our heartfelt gratitude to all who have stood by us, whether through prayers, well wishes, or physical presence.
In the pursuit of understanding and treating my father's illness, a series of tests revealed the devastating diagnosis of brain cancer. Subsequently, he embarked on a challenging course of radiation and other treatments.

Samson (Japi) Asfaw Meshesha
ሳምሶን (ጃፒ) አስፋው መሸሻ እባላለሁ። የአስፋው መሸሻ ልጅ ነኝ።
እንደሚታወቀው አባቴ እ.ኤ.ኤ ኦክቶብር ወር 2023 ዓ.ም በሥራ ላይ እያለ ድንገት በደረሰበት የጤና ችግር ምክንያት አክሶን ስትሮክ ማዕከል ሲረዳ ቆይቷል። ከዛም ለተጨማሪ ህክምና ወድ አሜሪካ በመምጣት፣ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ይገኛል።
በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሀገር ውስጥ ለህክምናው የሚያስፈለገውን ከፈተኛ የሆነ የህክምና ወጪ ሙሉ በሙሉ በመሸፈን እንዲሁም ደግሞ ለከፍተኛ ህክምና ከአጋዥ ነርስ ጋር አያይዞ ወደ አሜሪንካን ሀገር በማስመጣት፣ አዚህም ከመጣ በኋላ የተለያዩ ወጪዎችን በመሸፈን አባቴን በማስታመም ያለምንም ማወላወል የደገፈው፣ ያስታመመው በመሆኑ አባቴ ኢቤኤስን ሁሌም እንዳመሰገነው ይገኛል። እኔም አባቴ የኢቤኤስ ባልደረባ በመሆኑ ኩራት እንዲሰማኝ አድርጓል። በተጨማሪም አባቴ ሆስፒታል በተኛበት ወቅት የስራ ባልደረቦቹ፤ አንድም የቤተሰብ እገዛ ሳይፈልጉ በየተራ አብረውት በማደር ፍቅር በመስጠት ሳይሰለቹ በማስታመማቸው በመላው ቤተሰብ ስም አመሰግናለሁ። ከዚህ በተጨማሪም አባቴ ኢትዮጵያ እያለም ሆነ ወደ አሜሪካ ከመጣ በኋላ፣ ከአድናቂወቹ፣ ከህዝብና ከወዳጅ ጓደኞቹ ለጎረፈለት ፊቅርና ጸሎት ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
አባቴ እዚህ ከመጣ በኋላ በጆርጅ ዋሽንግተን ሆስፒታል የህመሙን መሰረታዊ መንስኤወች ለማወቅና ተጓዳኝ ህመሞችን በሚገባ ለመለየት፣ ብሎም ተገቢውን የህክምና መፍትሄ ተፈጻሚ ለማድረግ በምስልና ቴክኖሎጂ የታገዘና ናሙናወችንም በመውሰድ ተከታታይ ምርመራወች ተደርገውለት፤ በውጤቱም አባቴ የጭንቅላት ካንሰር እንዳለበት ተነግሮናል። ይሄንኑም ተከትሎ፣ ረጅምና አስቸጋሪ የሚባል የጨረርና የሌሎች ህክምናውችን መውሰድ ጀምሯል። ሂደቱ አዝጋሚና አድካሚ በመሆኑ አባቴ የ24 ሰዓት የነርስ ጥበቃና ክትትል እንደሚያስፈልገው፣ እንዲሁም ከመደበኛ ህክምናው ጋ ተያያሽዥ የሆኑ ክትትሎች ተጨማሪ ወጪ እንዳላቸው ተገልጾልኛል።
ስለሆነም እስካሁን ከአባቴ ጎን ያልተለያችሁት አድናቂወቹ፣ ወዳጅ ጓደኞችቹ ሁሉ በያላችሁበት በጸሎት እንድታስቡት፣ የምትችሉ ደግሞ በሃሳብም በገንዘብም ከጎኔ ሆናችሁ አባቴን እንዳስታምም እንድታግዙኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ። ለሁላችሁም፤ በአካልም፣ በመንፈስም፣ በጸሎትም አብራችሁት ላላችሁ ሁሉ የአባቴ የአስፋው መሸሻ ምስጋና ይድረሳችሁ።

Donations 

  • Anonymous
    • $50
    • 1 yr
  • Girmay Adhanom
    • $50
    • 1 yr
  • Canaan Anchbi
    • $50
    • 1 yr
  • Tewodros Gizachew
    • $10
    • 1 yr
  • meron girma
    • $30
    • 1 yr

Organizer

Samson Meshesha
Organizer
Washington D.C., DC

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee