Bahran's Medical Fund - ለልብ ታማሚ ልጃችን ድረሱልን!
Donation protected
ህጻን ባህራን ያሬድ ይባላል፡፡ የተወለደው ሰኔ 09 ቀን 2013 ዓ.ም ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት 4 ወር ከ8 ቀን ሆኖታል፡፡ በዚህ የዕድሜው ጠዋት Congenital (ኮንጀናይታል) heart disease ወይንም የልብ አፈጣጠር ችግር አጋጥሞታል። ህጻን ባህራን ያሬድ ባለፉት ወራት በጥቁር አንበሳ የልብ ህክምና ማዕከል እና በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የህክምና ክትትል ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም ከገጠመው ህመሙ መፈወስ አልቻለም፡፡ በመጨረሻም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በደብዳቤ ቁጥር ጳሀ8/1709 በቀን 15/02/2014 በሀገር ውስጥ እየተሰጠው ያለው ህክምና እንዳልተሳካ ገልፆልን ለከፍተኛ ህክምና ወደ ውጪ ሀገር ሄዶ መታከም እንደሚገባው አሳውቆናል፡፡
ውድ ኢትዮጵያውያን፣ እንደምታውቁት በልጅ መፈተን ፈተና ነው። ከባድ ነው። እኛም ቤተሰቦቹ በዚህ ከባድ ወቅት ላይ እንገኛለን። «50 ሎሚ ለ50 ሰው ጌጡ ነው» በሚለው ብሂል ተበረታተን ሸክማችንን አግዙን ልንል በየቤታችሁ መጣን። ለምታደርጉልን የገንዘብ ልገሳ፣ መልካም ምኞት እና ፀሎት ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን።
Bahran Yared was born on June 16, 2021. He is 04 months old now. He has congenital heart disease, a birth defect. He has followed up at St Paul hospital and Cardiac center at Black Lion Hospital. But we are told his treatment cannot be given in the facilities and that he has to go abroad for treatment with a letter number PH/1709 on October 27, 2021.
Dear Ethiopians, as you know, it's very hard to be challenged with a child's health. And we, his family, are facing this fate. We are knocking your houses to share our burden. We are whole heartedly grateful for your donations, good luck wishes and prayers.
Please donate any amount. And/or SHARE the link with your family and friends. We highly appreciate every support. Thank you!
Organizer
Tewedaj Adugna
Organizer
Dallas, TX