Support Muluken Melesse
Donation protected
እጅግ በጣም የተከበራቹ የጋሽ ሙሉቀን መኖር የሚያሳስባቹ ወገኖች በሙሉ እና በጸሎታቹ በገንዘባቹ ስታግዙ ለነበራቹ ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ አሁን ያለበት ሁኔታ በህክምና እየተረዳ ዊልቸር ላይ እቤት ከዋለ ብዙ ጊዜ ሆኖታል ። እንደሚታወቀው ከዚ በፊት በዚሁ ድህረ ገጽ መዋጮ ተጠይቆ ሁላችሁም ያቅማችሁን አግዛችሁታል እንዲሁም የማይለወጥ ፍቅር በተሰኘ የገቢ ማሰባሰቢያ ፈንድሬዝንግ ላይ የረዳችሁትን ሁላችሁንም ሳላመሰግን ኣላልፊም ለካስ እግዚአብሔር በየዘመናቱ የሚያዝኑና የሚራሩ ሰዎች አሉት ብዬ አምላኬን በየቀኑ ስለ እናንተ አመሰግነዋለው። ከዚህ በፊት በተሰበሰበው ገንዝብ ህክምናውን ሲከታተልና ለሚያስፈልጉት የተለያዩ ወጪዎች የተጠቀመበት ሲሆን ከዛ በፊት ከተለያየ 2 states $500 እና Ethiopian Evangelical Church $1000 በየወሩ ይረዳ የነበርው ሙሉ በሙሉ ከፈንድሬዝንጉ በሃላ የቆመ በመሆኑ ና እንዲሁም መንግስት ይረዳው የነበረውን የህክምና አርዳታ ሙሉ በሙሉ ስላቋረጠበት በአሁን ሰአት በከባድ ችግር ውስጥ ዪገኛል፣። በዚህ አጋጣሚ በብዙ አብራች የነበራቹ ሁላችሁም በተለይ ፓስተር ሀንፍሬ አሊጋዝ፣ ፓስተር ቶሎሳ ጉዲና አምላክ ከማያልቀው በረከቱ ዪባርካቹ። ውድ ኢትዮጵያውያን ጋሽ ሙሉቀንን በመርዳት ፍቅራችንን አንግለጽለት ወገን አለህ እንበለው ይህ ሰው ብዙ ዋጋ የከፈለ ሰው ነው!
Organizer
MULUKEN GESESSE
Organizer
Alexandria, VA