Help SAINT JOHN THE BAPTIST & ST ARSEMA MONASTERY
Tax deductible
ሥራ የሞላበት ትልቅ በር ተከፍቶልኛል
1ኛ ቆሮ 16፤9
በመካከለኛው የካልፎርንያ ግዛት የተቋቋመው የኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ገዳም በአጭር ግዜ የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል።
ይህም በዚህ አገር ተወልደው ለሚያድጉ ልጆች ልዩ ትኩረት ማድረግን መሰረት ያደረገ እንዲሁም አፋጣኝ ድጋፍ ለሚሹ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን አስቸኳይና የተሟላ አግልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ አማራጭ ሀሳብን ተግባራዊ ለማድረግ በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ እንገኛለን። የገዳሙን አገልግሎት በተለየ ሁኔታ ለልጆችና ለወጣቶች ተደራሽ ለማድረግ የምዕመናንን አስቸካይ ድጋፍ መጠይቅ ግድ ብሏል። በመሆኑም አቅማችሁ የፈቀደውን መጠን ለገዳሙ በመስጠት ይህን ትልቅ ዕራዕይ እውን ለማድረግ ትረባረቡልን ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ጥሪ እናቀርባለን። ለዚህ ታላቅ አገልግሎትና አላማ የሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆናችሁ ሁሉ አሻራቸውን በማስቀመጥ በታሪክ እና በትውልድ የማይረሳ ሕያው የሆነ ሥራ እንድትሠሩ እናሳስባለን።
Organizer
Saint JTBM Task Force
Organizer
Creston, CA
SAINT JOHN THE BAPTIST & ST ARSEMA ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO MONASTERY
Beneficiary