
Demiss Belete Appreciation and Family Support Fund
Tax deductible
የሀዘን እንጉርጉሮ
ደምስ በለጠ እዉነትን ተመርኩዞ በሚሰራው የጋዜጠኝነት ስራ ሁሌም የማደንቀው ነው። በዚህ ተግባሩ ህዝብ ማን ምን እንደሚሰራ እውነት የት ቦታ እንዳለ እንዲያውቅ በማድረግ ግዴታውን በአግባቡ ተወጥቷል። ደምስ ዛሬም እንደትናንቱ በእውነት ላይ ተመስርቶ የጋዜጠኝነት ተግባሩና በስፋት ለመቀጠል ብዙ ህልም ነበረው። ታዲያ ምን ያደርጋል ሞት ቀደመው!
ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ለዐማራ ልጆችና አንደነቷ ለጠነከረች እናት ሀገር ኢትዮጵያ በቆራጥነት ሲሟገት ኖሮ መስዋእትነት ከፍሏል። ቤተሰቡን በተለይም እራሳቸውን ያልቻሉ ልጆቹን በመርዳት ለጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ያለዎትን አክብሮትና ምስጋና ይገልጹ ዘንድ በማክበር እናሳስበዎታለን። ነፍሱን ይማርልን
የኢትዮጵያን አንደበት እዉቁ ጋዜጠኛ
ላይነቃ አሸለበ ለሊት እንደተኛ
መራር ነው ሀዘኑ ከአንጀት የማይወጣ
የዐማራውን ልሳን ደምስን ስናጣ
ኢትዮጵያ አገራችን በጠላት ተከባ
በክፉ ጎጠኞች ስትሆን ሰለባ
ህዝባችን ተከፍቶ በአለም ላይ ሲያነባ
ሰላሳ አመት ኖረ ድምፁን ሲያስተጋባ
የዐማራ ድምፅ ሁኖ ሞረሽን ወክሎ
ደምስ ተፋለመ በብዕር ተጋድሎ
አማራ ሲሳደድ በኢትዮጵያ አገሩ
ወንዶች ሲኮላሹ ሴቶች ሲደፈሩ
ማምከኛ ሲወጉ በግፍ ሲባረሩ
ርስቱን ሲቀማ ድንበሩ ሲደፈር
ጉበት ኩላሊቱ ብርንዶ ሲመተር
ቀድሞ ደርሶ ነበር ገና ከጅምሩ
በመረዋ ድምፁ በሰባ ብዕሩ
ቀደምት ታሪክን እውነትን ተንትኖ
ሀሰትን አጋልጦ የዐማራው ድምፅ ሁኖ
ለአመታት ሳይታክት ስደት ሳይበግረው
እውነትን ጎርጉሮ ሲያወጣ የኖረው
ባለ ብሩህ ተስፋ ባለ ብዙ ውጥን
ያልተዘመረለት ጀግናው ወንድማችን
እንደዋዛ አጣነው ጠፋ ከጎናችን
የቁርጥ ቀን ልጅ ነው ደምስ በለጠ
ለአገር ለወገኑ ራሱን የሰጠ
ኩሩው ኢትዮጵያዊ የወገን ጠበቃ
የደምስ ትንፋሽ ተቋረጠ አበቃ
ለብዙ ያጨነው ተስፋ የጣልንበት
እውቁ ጋዜጠኛ ባለ ርትዑ አንደበት
ደምስ ተለየን አጣነው በድንገት
በስደት የኖረው ለ30 አመት
በአርበኝነት ነበር በመንከራተት
አገሩ በገባ በጥቂት ቀናት
ወር እንኳን ሳይሞላው ባደገበት ቤት
ቤተሰቡ ሁሉ ሲያየው በስስት
ናፍቆቱን ሳይጨርስ አይተው ሳይጠግቡት
አሮጊት እናቱን ሳይሰናበት
ጨቅላ ወንድ ልጁን ከጎኑ አስተኝቶ
ድንገት ተሰወረ ሁሉን ነገር ትቶ
እንቆቅልሽ ሆነ የአሟሟቱ ነገር
እንቁ ኢትዮጵያዊ አጣን በዚች ምድር
ምርጡ ጋዜጠኛ በድንገት ተረታ
የምንመድበው ከአርበኞቹ ተርታ
ህያው ታሪክ አለው እሱ ቢያንቀላፋ
ለትዉልድ የሚቀር የሚታይ በይፋ
ነፍስህን በገነት ያኑርልን ጌታ
ዋጋህን ይክፈልህ ለዋልከዉ ዉለታ።
(ግጥም፥ ወ/ሮ ዘውዲቱ የማነ)
ደምስ በለጠ እዉነትን ተመርኩዞ በሚሰራው የጋዜጠኝነት ስራ ሁሌም የማደንቀው ነው። በዚህ ተግባሩ ህዝብ ማን ምን እንደሚሰራ እውነት የት ቦታ እንዳለ እንዲያውቅ በማድረግ ግዴታውን በአግባቡ ተወጥቷል። ደምስ ዛሬም እንደትናንቱ በእውነት ላይ ተመስርቶ የጋዜጠኝነት ተግባሩና በስፋት ለመቀጠል ብዙ ህልም ነበረው። ታዲያ ምን ያደርጋል ሞት ቀደመው!
ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ለዐማራ ልጆችና አንደነቷ ለጠነከረች እናት ሀገር ኢትዮጵያ በቆራጥነት ሲሟገት ኖሮ መስዋእትነት ከፍሏል። ቤተሰቡን በተለይም እራሳቸውን ያልቻሉ ልጆቹን በመርዳት ለጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ያለዎትን አክብሮትና ምስጋና ይገልጹ ዘንድ በማክበር እናሳስበዎታለን። ነፍሱን ይማርልን
የኢትዮጵያን አንደበት እዉቁ ጋዜጠኛ
ላይነቃ አሸለበ ለሊት እንደተኛ
መራር ነው ሀዘኑ ከአንጀት የማይወጣ
የዐማራውን ልሳን ደምስን ስናጣ
ኢትዮጵያ አገራችን በጠላት ተከባ
በክፉ ጎጠኞች ስትሆን ሰለባ
ህዝባችን ተከፍቶ በአለም ላይ ሲያነባ
ሰላሳ አመት ኖረ ድምፁን ሲያስተጋባ
የዐማራ ድምፅ ሁኖ ሞረሽን ወክሎ
ደምስ ተፋለመ በብዕር ተጋድሎ
አማራ ሲሳደድ በኢትዮጵያ አገሩ
ወንዶች ሲኮላሹ ሴቶች ሲደፈሩ
ማምከኛ ሲወጉ በግፍ ሲባረሩ
ርስቱን ሲቀማ ድንበሩ ሲደፈር
ጉበት ኩላሊቱ ብርንዶ ሲመተር
ቀድሞ ደርሶ ነበር ገና ከጅምሩ
በመረዋ ድምፁ በሰባ ብዕሩ
ቀደምት ታሪክን እውነትን ተንትኖ
ሀሰትን አጋልጦ የዐማራው ድምፅ ሁኖ
ለአመታት ሳይታክት ስደት ሳይበግረው
እውነትን ጎርጉሮ ሲያወጣ የኖረው
ባለ ብሩህ ተስፋ ባለ ብዙ ውጥን
ያልተዘመረለት ጀግናው ወንድማችን
እንደዋዛ አጣነው ጠፋ ከጎናችን
የቁርጥ ቀን ልጅ ነው ደምስ በለጠ
ለአገር ለወገኑ ራሱን የሰጠ
ኩሩው ኢትዮጵያዊ የወገን ጠበቃ
የደምስ ትንፋሽ ተቋረጠ አበቃ
ለብዙ ያጨነው ተስፋ የጣልንበት
እውቁ ጋዜጠኛ ባለ ርትዑ አንደበት
ደምስ ተለየን አጣነው በድንገት
በስደት የኖረው ለ30 አመት
በአርበኝነት ነበር በመንከራተት
አገሩ በገባ በጥቂት ቀናት
ወር እንኳን ሳይሞላው ባደገበት ቤት
ቤተሰቡ ሁሉ ሲያየው በስስት
ናፍቆቱን ሳይጨርስ አይተው ሳይጠግቡት
አሮጊት እናቱን ሳይሰናበት
ጨቅላ ወንድ ልጁን ከጎኑ አስተኝቶ
ድንገት ተሰወረ ሁሉን ነገር ትቶ
እንቆቅልሽ ሆነ የአሟሟቱ ነገር
እንቁ ኢትዮጵያዊ አጣን በዚች ምድር
ምርጡ ጋዜጠኛ በድንገት ተረታ
የምንመድበው ከአርበኞቹ ተርታ
ህያው ታሪክ አለው እሱ ቢያንቀላፋ
ለትዉልድ የሚቀር የሚታይ በይፋ
ነፍስህን በገነት ያኑርልን ጌታ
ዋጋህን ይክፈልህ ለዋልከዉ ዉለታ።
(ግጥም፥ ወ/ሮ ዘውዲቱ የማነ)
Organizer
ደምስ በለጠ መታሰቢያ
Organizer
Collierville, TN
Moresh Wegenie Amara Organization Inc
Beneficiary