በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ በህዝብ መዋጮ የሚሰራውን ፊልም አግዙ!
Donation protected
አርቲስት ሄኖክ ወንድሙ ማሞ እባላለሁ። በኢትዮጵያ ሲኒማ ዘርፍ የተሰማራሁ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ ከ 25 በላይ ፊልሞችን በዋና ገፀ ባህርይ ተውኛለሁ። በአዘጋጅነት (directing) ከ10 በላይ የሙዚቃ ቪድዮዎችን ሰርቻለሁ።
በኮቪድ ወረርሽኝ እና ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረዉ ጦርነትና ተያያዥ የማኅበራዊ ቀውስ የተነሳ፣ የፊልሙ ኢንዱስትሪ ኘሮዲዉሰር እና ተመልካች አጥቶ በመቆየቱ፣ ደረጃውን የጠበቀ ሥራ ለመስራት የሚደረገውን ጥረት ስለጎዳው፣ በእጅጉ ተቀዛቅዞ፣ መጥፋት ወደ ሚባል ደረጃ እየሄደ ይገኛል። ስለዚህም የጥበብ ሥራ ባለድርሻ አከላት ሁሉ የሚችሉትን ጥረት ሁሉ በማድረግ፣ ገና በደንብ ሳይጠነክር በፊት ወደ መጥፋት የተንደረደረውን የኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ መደገፍ እና ለማኅበረሰብ ጥራት ያለው ሥራ ለመስራት በሚችሉት ሁሉ መጣር አለባቸው ብዬ አስባለሁ።
እኔም ችግሩ በቀጥታ እንደሚያሳስበው ባለሙያ፣ በኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ዘርፍ አድናቆት እና ክብር እንዳገኘ ሰው፣ ከማኅበረሰብ የተቀበልኩትን ፍቅር ለመመለስ በማሰብና ያለውን መቀዛቀዝ ይቀርፋል ብዬ ያሰብኩትን ጥሩ ታሪክ ጽፌ ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ ጀምሬያለሁ። ይኼ ፕሮጀክት ሙያዬን እና ተመልካቹን በማክበር ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን አስቤያለሁና፣ የእናንተን የወዳጆቼ ቀና እገዛ እና የባለቤትነት ስሜት ስላስፈለገኝ፣ ይኽንን የገቢ ማሰባሰቢያ አዘጋጅቻለሁ።
የዚህ ፕሮጀክት የጋራ ባለቤቶችም እናንተው ናችሁ። የምትችሉትን በማዋጣት፣ የአገራችን ፊልም ያለበትን ሁኔታ ለመለወጥ፣ እኔ በገባኝ መጠን ያቀረብኩትን ሀሳብ በመደገፍ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ በአክብሮት እጠይቃለሁ። የዚህ ፕሮጀክት እንቅስቃሴም ሌሎች አርቲስቶችንም እንደሚያነቃቃም አምናለሁ።
ሌሎች ወዳጆችም የፊልም ኢንዱስትሪውን እንዲደግፉ፣ መልእክቱን በማሰራጨት አግዙኝ።
አመሰግናለሁ።
I, artist Henok Wondimu Mamo, am working in Ethiopian cinema as an actor and director. So far, I have been casted as a main character to more than 25 movies and participated in more than 10 music videos as a director.
Due to the global Covid pandemic and the war in Ethiopia and other related social complications, the Ethiopia film industry has suffered from lack of audience and producers; in effect, it has negatively impacted the effort of contributing standard movies towards waning. Thus, I believe that all stake holders of Ethiopian art should try their best to contribute high quality works to the audience and to save the Ethiopian film industry that is at risk of dying while there was a long way for it to an entrenched stage.
As an artist who has earned immense recognition in Ethiopian art and is deeply concerned about the situation, I am working to film a story - that I believe would contribute to an impetus to the industry from its current latent status and would ignite a light – to pay the appreciation I have received forward. In this regard, I have started this crowdfunding as I need your kind support and sense of ownership of the project.
You are going to be the owner of this project, and I believe the outcome of this project will be a great motivation to other artists. Please contribute any amount and support my initiative of contributing to change the status of Ethiopian film industry. Spread the word; share it with your friends.
Thank you!
Click the link below to watch a quick video about this fundraising event
Organizer
Henok Wendmu
Organizer
Melissa, TX