Journalist Askale Tesfaye medical expense
Donation protected
ጋዜጠኛ አስካለ ተስፋዬን እናግዝ
....
ገና በልጅነት እድሜዋ የልጆች ፕሮግራም አዘጋጅ ሁና ነው የጋዜጠኝነትን ህይዎት የተቀላቀለችው፡፡ ብዙዎቹ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ሬድዮ ላይ ‹ አስካለ ተስፋዬ ነኝ › በሚለው ቀጭን እና ተስረቅራቂ ድምጽ ያስታውሷታል፡፡
አስካለ ተስፋዬ ከልጅነት እድሜዋ ስትሻገር ወደ መዝናኛ ክፍል በመቀላቀል በኢትዮጵያ ሬድዮ ተወዳጅ በሆኑት
- ህብር ኢትዮጵያ
- የዘፈን ምርጫ
- ለወጣቶች
- የባህል ሙዚቃና
- ሰዎች እና ስራዎቻቸው
- የተሰኙ ተወዳጅ ፕሮግራሞች ላይ ለበርካታ አመታት በመስራት በአድማጮች አንቱታን ማትረፍ ችላለች፡፡
በዚህ መሃል ከአምስት አመት በፊት ከፍተኛ የወገብ ህመም ገጥሟት የነበረ ሲሆን በህክምና ለአንድ ዓመት ያህክል አልጋ ላይ ተኝታ ስትረዳ ከቆየች በኋላ ወደ ስራ ተመልሳለች ፡፡
ወደ ስራ ስትመለስም ከህመሙ ሙሉ ለሙሉ ያገገመች ባይሆንም ለሙያዋ ካላት ትልቅ ፍቅር የተነሳ ወገቧን በሜዲካል ቀበቶ አስራ እና በየ ሁለት ወሩ የማስታገሻ መርፌ በ 5500 ( አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር ) እየተወጋች ትልቅ ድካም እና ጥንካሬ ለሚፈልገው ‹ውሎ አዳር› ለተሰኘው ፕሮግራም ራሷን አዘጋጀች፡፡
በውሎ አዳር ፕሮግራምም ለህመሟ ሳትጨነቅ ለሙያ ቅድሚያ ሰጥታ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች የሚኖሩ ወገኖቻችንን ሕይዎት በተግባር ለማየት እና ለተመልካች ለማሳየት ያልወጣችው ዳገት ፤ ያልወረደችው ቀልቁለት ያላየቸው የሃገራችን ክፍል የለም፡፡
40 የሚደርሱ የሃገራችን አካባቢዎች በማምራትም የበሉትን በልታ፤ የለበሱትን ለብሳ የሃገሯን ውበት ለማስተዋወቅ ከህመሟ ጋር እየታገለች ብዙ ለፍታለች ። አሁን ግን አልቻለችም፡፡ ሁሉም ነገር ከአቅሟ በላይ ሁኖባታል፡፡ በጭንቅላትዋ ላይ በተፈጠረ የጤና ችግር ምክኒያት ቤት ከዋለች ሰነባብታለች፡፡
ህመሟም በሃገራችን ሊታከም ባለመቻሉ ወደውጭ ሃገር ሄዳ መታከም አንዳለባት ተገልጾላታል፡፡
ይህን ህክምና በራሷ ወጭ ለመታከም ደግሞ አቅሟ የሚፈቅድ ባለመሆኑ የናንተን እገዛ ትሻለች፡፡
ይችን የኢትዮጵያዊ መልክ መገለጫ የሆነች ተወዳጅ ጋዜጠኛ በማገዝ ፤ ወደ ምትዎደውና ወደምንዎደው ስራዋ እንድትመለስ ለማድረግ የሁላችንም ሃላፊነት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የሂሳብ ቁጥር ፤ 1000189582505
አስካለ ተስፋዬ
ለበለጠ መረጃ
በስ.ቁ 7203430385
0911 33 56 56
0913 36 23 78
0911 86 74 50
ይደውሉ።

Organizer
Miky Ab
Organizer
Aurora, CO