
ለአቶ ወንድወሰን ተሾመ መኮንን በህይወት ዘመኑ ላበረከተው ሀገራዊ አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት!
Donation protected
ለሀገርና ለወገኑ ጥልቅ ፍቅር ያለው ጀግናው ወንድማችን አቶ ወንድወሰን ተሾመ መኮንን ባደረበት ሕመም ገና በለጋ እድሜው በአጭር ተለይቶናል። ወንድወሰን በሰሜን አሜሪካ ላለፉት እረጅም አመታት በሀገር ውስጥ በአንባገነናዊ አገዛዝ ለሚማቅቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀን ከሌት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ገንዘቡን ግዜውንና ሙሉ አቅሙን ለትግሉ ሲያበረክት የኖረ ግንባር ቀደም የመብት ታጋይ ነበር። ወንድማችን ወንድወሰን በሰሜን አሜሪካ ዝነኛ የነሆነውን የታጋዮች ሕብረት የዲሲ ግብረ ሃይል ከምስረታው አንስቶ በአመራር እና አባልነት ከፍተኛ ተጋድሎ ሲያደርግ ቆይቷል:: በአማራው ሕዝብ ላይ የተከፈተውን የሕልውና ትግል በውጭ የድጋፍ ድርጅቶች ውስጥ በመሳተፍ በርካታ አስተዋጽዖ እያደረገ የቆየ እና ሕይወቱ እስካለፈበት ቀን ድረስም በአመራር እና በአባልነት የሚጠበቅበትን ተሳትፎ እያደረገ ቆይቷል። ይህ ጀግና ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት ነበር። ወንድማችን ለሀገሩና ለወገኑ ገንዘቡንና ግዜውን ሳይሰስት በማበርከት የዜግነት ድርሻውን ከሚገባው በላይ ለከፈለልን ታጋይ ስላደረገው ታላቅ ሀገራዊ አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠትና ለማመስገን ይህን የጎፈንድሚ አካውንት ከፍተናል።
የትግል አጋሮቹ እና ጓደኞቹ!
Organizer
Selamawit Gebremariam
Organizer
Sterling, VA