Let's save Tewodros Asgedom
Donation protected
ቴዎድሮስ አስግዶም Taddy Asegedom በተጨዋችነት ዘመኑ በድንቅ ችሎታው ብዙዎቻችንን አስደምሞናል፡፡ በመልካም ባህሪውና ፀባዩም ጭምር ተለይቶ ይታወቃል፡፡ ሐረር ቢራ፣ አዳማ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ትራንስ ኢትዮጵያ፣ መድን እና በሌሎችም በርካታ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በመጫወት አሳልፏል፡፡ ኳስ ካቆመ በኋላ በግል ስራ ሲተዳደር ቆይቷል፡፡ ይሁንና በድንገት ያጋጠመው ህመም ህይወቱን ከባድ አደጋ ላይ ጥሎታል፡፡
የእግር ኳስ ተጨዋቹ ቴዎድሮስ አስግዶም በአሁኑ ወቅት ሬክታል ሲኤ በተባለ ህመም እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ ይህም ማለት የመፀዳጃ አካሉ ላይ የተፈጠረ ካንሰር ነው፡፡ በዚህም መሰረት የመፀዳጃ አካሉ ተቆርጦ እስከመጨረሻው በኮሎስቶሚባግ እንዲጠቀም ይገደዳል ማለት ነው፡፡ እስካሁን በሀገር ውስጥ ባደረገው የህክምና ክትትል በታች በኩል ያለው የአንጀት ክፍሉ ሙሉ ለሙሉ ተቆርጦ በመውጣት በጎን በኩል እንዲፀዳዳ ብቻ ማድረግ እንደሚችል ተነግሮታል፡፡ ነገር ግን ወደ ውጪ ሀገር ቢያመራ የአንጀት ክፍሉን ቆርጦ ከማውጣት ይልቅ ቀዶ ጥገና በማድረግ ወደ ቀድሞ የመፀዳጃ ስርዓቱ መመለስ እንደሚችል ማረጋገጫ ተሰጥቶታል፡፡
ቴዎድሮስ አስግዶም እስካሁን በሀገር ውስጥ ባደረገው ህክምና የመጀመሪያ ሰርጀሪ አድርጎ በጎን በኩል እየተፀዳዳ እና የኮሞቴራፒ ክትትል እያደረገ ይገኛል፡፡ በቀጣይም ተጨማሪ የኮሞቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ ህክምና ማድረግ ይቀረዋል፡፡ ነገር ግን በቋሚነት ህይወቱን ለማትረፍ ወደ ውጪ ሀገር ሄዶ ዘላቂ ህክምና ማድረግ አስፈልጎታል፡፡ ለዚህም በህንድ ሀገር የሚገኘው አስቴር ሆስፒታል 15 ሺህ ዶላር እንደሚያስፈልገው ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለለት ለሚገኘው ለኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶስዬሽን አስታውቋል፡፡
በመሆኑም የተጨዋቹን ህይወት ለማትረፍ የሁላችንም ርብርብ አስፈልጓል፡፡ ስለዚህ በሚከተለው የባንክ ቁጥር የአቅማችንን ያህል ድጋፍ በማድረግ የዚህን ተጨዋች ህይወት እንታደገው፡፡ ተጫውቶ ያሳለፈባቸው ክለቦች፣ አብረውት የተጫወቱ፣ የእግር ኳስ አፍቃሪያን፣ በሀገር ውስጥና በባህር ማዶ የምትገኙ ወዳጆቹና ልበ ቀና ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከጎናችን እንደምትቆሙ እርግጠኞች ነን፡፡ ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ጌጡ ነው፡፡ ስለዚህ የአቅማችንን በማድረግ ወንድማችንን እንታደገው፡፡ መረጃውንም ሼር በማድረግ ሌሎችም እናድርስ፡፡ ሁሉም የሚዲያ ባልደረቦቻችንም ዜናውን ለታዳሚዎቻችን በማድረስ የበኩላችንን ጥረት እንድናደርግለት በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ በእናንተም ሙሉ ዕምነት አለኝ፡፡
Tewodros Asegedom Taddy Asegedom has amazed many of us with his amazing skills. He is also known for his good character and behavior. He has spent his time playing for Harar Beer, Adama City, Ethiopia Coffee, Trans Ethiopia, Medin and many other premier league clubs. After he stopped playing football, he has been managing a private job. The sudden pain he faced has made his life difficult. He dropped it on the deck.
Football player Tewodros Asgedom is currently suffering from rectal ca. Which means it is a cancer that is caused on his reproductive organs. According to this, his reproductive organs will be cut off and forced to use colostomybag for the rest of the time. So far, according to the medical treatment he has done in the country, his intestine has been completely removed from the side. Clean He has been told that he can only do it. But if he goes abroad, he has been assured that he can go back to his old toilet system by surgery rather than cutting out his intestine.
Tewodros Asgedom has undergone his first domestic surgery and is being cleaned on the side and undergoing chemotherapy. He still has to do more chemotherapy and radiotherapy. But to save his life he needs to go abroad for permanent treatment. Therefore, Aster Hospital in India has donated 15 thousand dollars The case that matters most The Ethiopian Professional Footballers Association has announced that he is being closely monitored.
Therefore, to save the lives of the players, we need all of our cooperation. Therefore, let's save the life of this player by donating to the following bank number as much as we can. The clubs he played with, the players he played with, football lovers, his friends living in the country and abroad and all the good-hearted Ethiopians will stand by us. Fifty lemons for one person. The load is the ornament for fifty persons. So let's save our brother by doing what we can. Let's share the information and spread it to others. I respectfully request all our media colleagues to do our part by delivering the news to our audience. I have full faith in you.
Organizer
Mekonen Kassa
Organizer
Washington D.C., DC