Medical expense For Belay Zenebe
Donation protected
ወንድማችን በላይ ዘነበ ተወልዶ ያደገው በራያ-ኣላማጣ ልዩ ስሙ ፋጫ-ሃራ ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ ለሙዚቃ ያለው ፍቅር ልዩ ነበር። በዛ በሚያምረው ሸጋ ድምፁ ጉማየ... ጉማየ እያለ ስያንጎራጉር የራያ ጎበዞች እና የራያ ወይዛዝርት በሙዝቃው ፍቅር ልባቸውን ያሸፍተው ነበር። የሙዝቃው ስራው በታዳጊዋ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚኒሚድያ ክበብ ሀ ብሎ ጀመረ። በኋላም ኣላማጣ ከተማ በሚገኘው የሙዚቃ ቡድን( ትግስት ባንድ) ተቀላቅሎ ስራዎቹ ያቀርብ ነበር። ከፍ ስልም በመቀሌ በሚገኘው የኪነት ባንድ የራያ ዘፈኖቹ ይዘፍን ነበር። ከተወዳጅ ዘፈኖቹ መሃከል: ጉማየ: ዋራሞዋ: ፈልጋ የመሳሰሉትን ሸጋ ዘፈነቹን አበርክቷል ።
በላይ ዘነበ የራያ ባህል እንድያድግ እንዲሁም ለራያ ወጣት ዘፋኞች አርአያነት የነበረ ወንድማችን ነው። ሁኖም ግን ላለፉት ሁለት ሶስት አመታት በጠና ታሞ ከቤት አይወጣም። ቤተሰቦቹም የቻልቱን ያህል ህክምናም ፀበልም ወስደውታል። ነገር ግን በቀላሉ ሊድን አልቻለም። ወደ ተሻለ ህክምና ሂዶ እንድታከም ቤተሰቦቹ አቅም የላቸው። ሰውን ለመረዳት ሰው መሆን በቂ ነውና ለዚህ ሸጋ ወጣት አቅማችን በፈቀድው እንርዳው። በላይም ወደ ነበረበት እንድመለስ የእግዚአብሔር ፍቃድ ይሁን ኣሜን!

Organizer
Getachew Nigus
Organizer
Chicago, IL