Main fundraiser photo

Mekane Sebhat Kidist Selassie Fundraising

Tax deductible
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።

ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤
ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ።
ማቴ 6:19-20

የሳክራሜንቶ መካነ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በ2020 የተመሰረተ ሲሆን ቤተ ክርስቲያን በመከራየት በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የቤተ ክርስቲያኑን መገልገያ ንዋየ ቅድሳት በማሟላት፣ በሃገረ አሜሪካ ተወልደው ያደጉ ልጆችን በቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንዲታነጹና ዲቁናን እንዲቀበሉ በበቂ እውቀት በማስተማር፣ አዳዲስ ዲያቆናትን በማሰልጠን፣ የህጻናት ፣የወጣቶች እና የአዋቂዎች ሰንበት ትምህርት ቤት በመመስረት ሰፊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል:: በተጨማሪም በአባላት ጥንካሬ ፣ መንፈሳዊ እውቀት ፣በጾም ፣በጸሎት ፣ በጥበብ ፣ በሃሳብ እና በጉልበት በልዩ ልዩ የወንጌል አገልግሎት እንዲያድግና እንዲሰፋ ቤተ ክርስቲያን መግዛት አስፈላጊ በመሆኑ ላቀድነው ዓላማ የሚስማማ 3 ኤከር የሚሆን ቦታ ከትልቅ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ጋር በካሊፎርንያ መናገሻ ከተማ በሳክራሜንቶ ውስጥ በቀን 26/07/2016 ዓም ተገዝቷል:: ስለሆነም ይህ ታላቅ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ባሉት ጠንካራ የቤተ ክርስቲያን ምእመናን የተገዛ ቢሆንም ብዙ ስራ የሚጠይቅ፣እንዲሁም ከፍተኛ ሞርጌች ክፍያ ያለው ስለሆነ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት እንዲሳተፉ እና በረከትም እንዲያገኙ ይህንን ጎፈንድሚ ከፍተናል። ስለሆነም በከተማችን ያለውን ማኅበረሰብ በተለያየ የህፃናት ፣ የወጣቶች ፣ የጎልማሶች ፣ የአዛውንት ፣ እንዲሁም የሴቶችና የቤተሰብ ክርስቲያናዊና ማህበራዊ ኑሮን የሚጠቅም አገልግሎት በየፈርጁ ለማቅረብ አቅዷል:: አገልጋዮችም በእውቀትና በጥበብ የሚያድጉበት ህዝብና አገርን የሚያገለግሉ እግዚአብሔርንም የሚፈሩ መንፈሳውያን አገልጋዮች የሚወጡበት የእግዚአብሔር ቤት እንዲሆን በእናንተ በውድ ምእመናንና ለጋስያን ያሉብንን ችግሮች ባጭር ጊዜ እንደሚቀረፍ በመተማመን የኦርቶዶክሳውያንና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች የሆናችሁ ሁሉ እቅዳችንን እውን ለማድረግ እንድታግዙንና የዚህ ታላቅ ታሪክ ተካፋይ እንድትሆኑ እንጋብዛለን:: ለምታደርጉልንም ትብብር በሥላሴ ስም እናመሰግናለን።

የደብሩ ሰበካ ጉባኤ እና ልማት ኮሚቴ

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ሃገራችን እና ህዝባችንን ይጠብቁልን።


ማሳሰቢያ

እርዳታ በሚያደርጉበት ጊዜ (GoFundMe የሚጠይቅዎትን ተጨማሪ ችሮታ (ቲፕ) መክፈል አይኖርብዎትም። ተጨማሪ ችሮታው (ቲፕ) ወደ መካነ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አካውንት ገቢ አይሆንም። ስለዚህ ቲፕ ሳይጨምሩ እርዳታዎን ለመስጠት የሚከተለውን ያድርጉ፤ ‘በቲፑ ሳጥን ውስጥ ዜሮ (0.0) ከሞሉ በኋላ የእርዳታውን ገንዘብ በእርዳታው ቦታ ብቻ ይሙሉ::


የሥላሴ በረከት ከሁላችን ይሁን።

In the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, One God. Amen.

Matthew 6:19-20
19 “Do not store up for yourselves treasures on earth, where moths and vermin destroy, and where thieves break in and steal. 20 But store up for yourselves treasures in heaven, where moths and vermin do not destroy, and where thieves do not break in and steal."

Mekane Sebhat Kidist Selassie Ethiopian Orthodox Tewahedo Church was founded in 2020. In a short time, our church has shown remarkable growth. We rented a place of worship and have been holding weekly services, while also establishing Sunday school programs for children, youth, and adults. Through the teachings of the Word of God, we've been nurturing and strengthening our members.

Notably, we've successfully ordained deacons from our youth group, and they are now actively serving our church community. However, our dreams don't stop here.

In March 2024, the church purchased a building with 3-acres of land in Sacramento, California suitable for our purposes. The church was bought by the strong commitment of the believers, through prayers and hard work. However, the building is old and needs a lot of renovation and maintenance in addition to the large mortgage payments. To cover these expenses, we created this gofundme effort to raise funds by reaching out to all contributors who are followers of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church as well as all of our friends in Christ.

The purpose of this church is to provide biblical guidance and services to all people who need them.

The church invites you all to participate in this holy purpose by making a contribution to be a part of this blessed purpose.

We thank you in the name of the Holy Trinity for your support and encouragement. Your support, no matter the size, makes a huge impact.

God bless you!

Please note that when making a donation, you can change the tip amount to $0.00 because the tip does not get paid to the church. You can just enter the amount of your donation into the donation entry field.
Donate

Donations 

  • Anonymous
    • $100
    • 8 mos
  • Anonymous
    • $240
    • 9 mos
  • Anonymous
    • $20
    • 10 mos
  • Anonymous
    • $50
    • 10 mos
  • Naod N
    • $250
    • 10 mos
Donate

Organizer

Mekane Sebhat Kidist Selassie Church
Organizer
Florin, CA
Mekane Sebhat Kidist Selassie Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
Beneficiary

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Our Trust & Safety team works around the clock to keep our community safe