Main fundraiser photo

St Gabriel Catholic Parish in Addis Ababa

Tax deductible


2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9:8-11 በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።
ለዘሪ ዘርን ለመብላትም እንጀራን በብዙ የሚሰጥ እርሱም የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል ያበረክትላችሁማል፥ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል፤
በእኛ በኩል ለእግዚአብሔር የምስጋና ምክንያት የሚሆነውን ልግስና ሁሉ እንድታሳዩ በሁሉ ነገር ባለ ጠጎች ትሆናላችሁ።

ከሳምንታት በፊት በካህናትና በዲያቆናት መኖሪያ ቤት ላይ ከእኩለ ሌሊት በኋላ በተነሳው ድንገተኛ የኤሌክትሪክ የእሳት አደጋ ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመትን አስከትሏል፡፡ ሆኖም በዚህ አደጋ በሰው ላይ የአካል ጉዳት ባለመድረሱ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ የዚህን እሳት አደጋ ያደረሰው  ውጤት ፎቶ ይመልከቱ፡፡ 

የኮንሶላታ ሚስዮናውያን ገዳም የነበረው፣ አዲስ አበባ ጉለሌ አካባቢ ራስ ደስታ ሆስፒታል (ቀድሞ ሐኪም ቦራ በመባል የሚታወቀው) አጠገብ የሚገኘው የአሁኑ ቅዱስ ገብርኤል ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ደብርና ዘርዓ ክህነት ትምህርት ቤት፣ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው  በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ጥንታዊ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ ነው፡፡ 
አሁን የሚታየው የቤተ ክርስቲያኑ የማስፋፋት ግንባታ ሥራ በ1920 ዓ.ም ቢጀመርም በተለያዩ ምክንያቶች ሳይጠናነቅ ረጅም ዓመታትን አስቆጥሮ ነበር::
ቤተ ክርስቲያኗን ውብ እንድትሆን ያደረጓት በርካታ የተተከሉ ረጃጅም ምሰሶዎች ክፍት እንደሆኑ ለ38 ዓመታት ያህል በመቆየታቸው የአካባቢው ታዳጊዎች ወደ ላይና ወደታች በመውጣትና በመውረድ ይዝናኑበት እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ መሆኑ የዚህን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ልዩ ያደርገዋል፡፡ 
የዘገየው ግንባታ ሥራ ሲጠናቀቅ፣ ይህ ውብ ቤተ ክርስቲያን ሰኔ 19 ቀን 1958 ዓ.ም.
በቀድሞው ንጉሥ በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና በአቡነ አሥራተ ማርያም ይምሩ በይፋ ከተመረቀ በኋላ:: እንዲሁም በፈረንሣዩ ፕሬዚደንት ቻርልስ ደጎል ተጎብኝቶዋል::የኅብረተሰቡ መንፈሳዊና ማኅበራዊ  አገልግሎት እንደገና ቀጥሎ እነሆ 55 ዓመታትን ለማስቆጠር በቅቷል፡፡

በአደጋው ምክንያት የታጣውን ንብረት ለመተካትና መኖሪያ ቤቱን መልሶ መገንባት ይቻል ዘንድ ሁላችንም የዋሺንግተን ዲሲ ኪዳነ ምሕረት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን፣ ክርስቲያን ወንድሞችና እህቶች፣ የእምነት አጋሮቻችን ሁሉ የድጋፍ ዕርዳታ እጆቻችሁን እንድትዘረጉ የዋሽንግተን ዲሲ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች፡፡ የቅዱስ ገብርኤል የደስታ ብሥራት አይለያችሁ::

እግዚአብሔር ሁላችሁንም ይባርክ፡፡ እናመሰግናለን::



2Cor 9:8-11
As it is written:
“He scatters abroad, he gives to the poor; his righteousness endures forever.”
The one who supplies seed to the sower and bread for food will supply and multiply your seed and increase the harvest of your righteousness you are being enriched in every way for all generosity, which through us produces thanksgiving to God.”         
Few weeks ago, St Gabriel Catholic Church lost its residential quarter of priests and deacons due to an accidental electrical fire which occurred at night that resulted in extensive damage of property.  Praise be to God for no one was physically hurt. Please see the pictures of this devastating fire outcome.
The present Parish of Saint Gabriel Catholic Church used to be also seminary school situated in Gulele near Ras Desta Hospital (known as Hakim Bora) in Addis Ababa formerly established and run by the Monastery of Consolota missionaries is one of the oldest Catholic churches in Ethiopia.
The Church has a unique history; its construction started in 1928. For more than 38 years, erected pillars that made the church beautiful today were left open where the neighborhood children used to play on them. After its long awaited completion, the Church started to serve the community on June 26, 1966; following the official inauguration by the late Emperor Haile Selassie I & Abune Asrate-Mariam Yemiru. It was also visited by President Charles DeGaul of France.

The Kidane Mehret Ethiopian Catholic Church of Washington DC is calling on all parishioners, brothers and sisters in Christ and good wishers to extend their hands in support of rebuilding the residential quarter our fellow church community lost. May the intercession of St. Gabriel be with you all. 
God bless and thank you.
Kidane-Meheret

Organizer

Kidane-Mehret Church, DC
Organizer
Washington D.C., DC
Kidane-Mehret Geez Rite Catholic Church
Beneficiary

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Our Trust & Safety team works around the clock to keep our community safe