Main fundraiser photo

Strengthening Tsewa'e

Donation protected
በኢትዮጵያችን ውስጥ ያለው ፖለቲካዊ ምስቅልቅል እና ሃይማኖታዊ ሽኩቻ ሀገርን ለማፍረስ እየተዘጋጀ እንዳለ ድግስ መስሏል፡፡ ምስቅልቅሉ የሰላሟን ሥሮች ነቃቅሏሎ፣ ማኅበረሰባዊ መስተጋብሯን አፈናቅሎ ኢትዮጵያውያን በገዛ ሀገራቸው ከኹለተኛ ዜጋ በታች እንደኾኑ እስኪሰማቸው እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህንን በታሪካችን ገጽ በጥቁር ጠባሳነት የሚመዘገብ ሁኔታ በአጭሩ ለመቀልበስ መረጃ መስጠት እንዲሁም አቅጣጫ ማሳየት እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ ለዚህም ደግሞ የብዙኀን መገናኛ አገልግሎት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡

 

ጽዋዕም ይህንን አገልግሎት ለቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ለማበርከት የራሷን ድርሻ ኃላፊነት በተሰማው ደረጃ ለመወጣት ተፍ ተፍ እያለች ትገኛለች፡፡ ጥቅምት ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. ከተመሠረተች ወዲህ የተቻላትን አገልግሎት በመስጠት ላይ መኾኗ ይታወቃል፡፡ አገልግሎቷ ይበልጥ ይጠናከር ዘንድ የገንዘብ ዐቅሟን ማጠናከር አስፈላጊ ስለኾነ በጎ ፈቃድ ያላቸው ሁሉ ይደግፏት ዘንድ ይህ የጎፈንድሚ ሒሳብ (GoFundMe Account) ተከፍቷል፡፡ የቻላችሁትን ሁሉ በማድረግ ከጎናችን መቆማችሁን ታሳዩን ዘንድ በትሕትና እንጠይቃለን፡፡
Donate

Donations 

    Donate

    Organizer

    Abayneh Kassie
    Organizer
    New York, NY

    Your easy, powerful, and trusted home for help

    • Easy

      Donate quickly and easily

    • Powerful

      Send help right to the people and causes you care about

    • Trusted

      Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee