Support Gasha Amhara Dimts Radio - SW Broadcast
Tax deductible
ጋሻ አማራ በኢትዮጵያ አዲስ አመት ዋዜማ ጋሻ የአማራ ድምጽ ራዲዮ (ጋአድራ) የአጭር ሞገድ ስርጭት ጀምሯል። የቴሌቪዥን ወይም የኢተርኔት አገልግሎት የማግኘት እድል የሌላቸውን በተለይ በገጠር ለሚኖሩ ወገኖቻችንን የወቅታዊ መረጃ ተጠቃሚ ለማድረግ ታስቦ በኢትዮጵያና አካባቢው ላሉ አድማጮች የሚደርስ የአጭር ሞገድ ራድዮ ስርጭት ነው። ጋሻ አማራ በሀገር ውስጥም ይሁን በዲያስፖራ የሚንቀሳቀሱ ታማኝ የአማራ ሚዲያ አካላትን በማስተባብር የሚዘጋጁ ፕሮግራሞችን በስፋትም በጥልቀትም አጠንክሮ ለመቀጠል የተሟላ እቅድ ያለው ሲሆን፣ ለዚህ እውን መሆን ደግሞ በዲያስፖራ ያለው ኢትዮጵያዊ ወገናችን በተለይ አማራው ከፍተኛ ድጋፉን እንደሚሰጠን በመተማመን ነው። አገራችንን ቁልቁል እያወረዳት ያለውን፣ በተለይም በአምራው ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ የጋረጠውን የአፓርታይድ ሥራአት በተባበረ ህዝባዊ ኃይል ማስወገድ ይቻል ዘንድ በመረጃ የታጠቀነ የተናበበ ማህበረሰብ እንዲኖር የሚያግዝ የሚዲያ አገልግሎት አስፈላጉ መሆኑን የሚታወቅ ነው። በመሆኑ ይህ የጋሻ ድምጽ ራዲዮ እውነትን፣ ጽናትንና፣ ድፍረትን ታጥቆ የሚያደርገውን የአማራ ድምጽነት በእውቀት፣ በጊዜ እና በገንዘብ ይደግፉ ዘንድ ወገናዊ ጥሪያችን ነው።
Gasha Amhara (AFP-FAC) wants to join the effort to make a difference. We are raising money to benefit Gasha Amhara Dimts Radio. Thanks in advance for contributing to this cause, which means so much to the Amhara cause.
Organizer
Gasha Amhara
Organizer
Collierville, TN
Moresh Wegenie Amara Organization Inc
Beneficiary