Hauptbild der Spendenaktion

ጽርሐ ጽዮን ዘተዋሕዶ የአንድነት ኑሮ ማህበር

Spende geschützt
ጽርሐ ጽዮን ዘተዋሕዶ የአንድነት ኑሮ ማኅበር የሰባኪያነ ወንጌል ማሰልጠኛ ማዕከል ለቤተ ክርስቲያን የሚተኩ አገልጋዬችን በተለይ በጠረፍ አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖችን በቋንቋቸው የሰባኪያነ ወንጌል ስልጠናንና ግብረ ዲቁና እየሰጠ ቤተ ክርስቲያን ተተኪ አገልጋይ እንዲኖራት እየሰራ ይገኛል::
እስካሁን ከ52 ሀገረ ስብከት ከ76 ቋንቋ በላይ የሚናገሩ ከ1ሺህ በላይ አገልጋዬችን ለቤተ ክርስቲያን እና ለምእመናን ወንጌልን በቋንቋቸው የሚያስተምሩ ብቁ ዲያቆናትንና መምህራንን አፍርቷል::

ማኅበሩ ማነው?
- የቀደሙ አባቶቻችን ሐዋርያትን አሠረ ፍኖት (ፈለግ) ተከትሎ የካቲት 23 1980 ዓ.ም ጽርሐ ጽዮን ዘተዋሕዶ የአንድነት ኑሮ ማኅበር ተብሎ ተመሠረተ።

የማኅበሩ ዓላማዎች 
- ሥጋዊና መንፈሳዊ ሀብት አዋሕደን እርስ በእርስ በመረዳዳት፣ በመደጋገፍ፣ በሰላምና በፍቅር በመኖር ለኅብረተሰቡ አርአያና ምሳሌ መሆን
- ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት አቅማችን የፈቀደውን አስተዋጽኦ ማበርከት
- በልዩ ልዩ ችግሮች ላይ የወደቁትን የሰው ልጆች ይልቁንም የሃይማኖት ወገኖችን መርዳት

ማኅበሩ እየሠራቸው ያሉ ሥራዎች
- ከኅዳር 21 ቀን 1985 ዓ.ም ጀምሮ 'መለከት መጽሔት'ን እያዘጋጀ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ምእመናን እያሰራጨ ይገኛል።
- ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ምእመናንን በማስተባበር  ለገጠሪቱ ቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚሰጡ ሰባኪያነ ወንገልን እያሰለጠነ ይገኛል።
- ደጋፊዎችን በማስተባበር ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ በአካባቢው ለሚኖሩ ረዳት ለሌላቸው አረጋውያን የዕለት ጉርስና የዓመት ልብስ እየሰጠ ይገኛል።
- ወላጅ አልባ ለሆኑና ቤተሰቦቻቸው በቂ መተዳደሪያ ለሌላቸው ልጆች የዓመት ልብስ፣ የዕለት ጉርስና የትምህርት መሣሪያዎችን አሟልቶ በማኅበሩ ት/ቤት በነፃና በግማሽ ዋጋ ለአካባቢው ኅብረተሰብ በአነስተኛ ክፍያ እያስተማረ ይገኛል።

የማኅበሩ ቀጣይ ሥራዎች
- የተጀመረውን ዘመናዊ የሰባኪያነ ወንጌል ማሠልጠኛ ሕንፃ ማጠናቀቅ
- አብነት መምህራንን በመቅጠር ተተኪ ዲያቆናትን፣ ቀሳውስትንና መምህራንን ማፍራት
- በቤተክርስቲያኒቱ ማሠልጠኛዎች የሚሰጠውን ትምህርት በማሰባሰብ ተመሳሳይ የሆነ ሥርዓተ ትምህርት ማዘጋጀት
- ችግር ባለባቸው በገጠሪቱ አብያተ ክርስቲያናት መምህራንን በመላክ ሰባኪያነ ወንጌልን በብዛት ማሠልጠን

የእኛስ ድርሻ?
- ማኅበሩን በጸሎት፣ በኃሳብና በገንዘብ መርዳት
- በተለይ በውጪው ዓለም ያለን ምእመናን ቢያንስ የአንድ ቀን የቡና ወጪያችንን ($10) ለዚሁ አገልግሎት በመርዳት ፈተና ላይ ያለችውን እናት ቤተክርስቲያናችንን እንታደግ       

የባንክ አካውንት ቁጥራችን -153699663404  (US Bank)
 
    "Tsereha-Tsion United Life Association." was established on March 2nd, 1988 by spiritual members of Sunday school and believers gathered from churches in Addis Ababa with the objective of the expansion of the gospel in accordance with the word of God in Acts of the Apostles 4:32-37.
 
                                           Objective
Some of the major objectives of the Association are:

1.    To pray to god in favor of world peace, and four the unity of church:
2.    To be exemplary to that society by leading a life of love, peace and by supporting one another combining our spiritual physical wealth:
3.    To contribute our share for the expansion of the gospel:
4.    To contribute our part of Christian share for the love of our country and for the respect of the citizens.
5.    To support the destitute, especially unto the who are of the household of faith.

                                                 Plan
If it is God’s will. In collaboration with other believers, to build well equipped modern Gospel Preachers’ Training center in order to extend the current two moths winter training to the year full-fledged all – rounded courses.

1.    To hire exemplary teachers (“ABINET MEMEHRAN”) so as to produce the would-be serving teachers, priests and deacons for the church:
2.    Organize along with the above center, a technical training’s unit for the trainee and also create finance resources for the training.
3.    Prepare and review curriculum by collecting educational material carried by the church.
4.    Create a research center by gathering high standard teachers, organizing their day to day need in order to keep on spiritual books to protect its followers from foreign anti-Christian Teachings.
5.    Train gospel preachers at rural and remote center of the country by organizing Field Training enter.  
6.    Support and follow up the trained members by sending teachers & spiritual singers to their respective area in order to strengthen the Gospel work continuously.


To date, this association has produced more that 1,365 qualified deacons and teachers who teach the gospel to the church and its followers in more than 76 languages. Please support us with your thoughts, education, money, and prayer.

Bank account -153699663404  (US Bank)
Spenden

Spenden 

  • Abebe Tesema
    • 100 $
    • 4 Jahre
  • Anonym
    • 500 $
    • 4 Jahre
  • Hilemariam Mammo
    • 1000 $
    • 4 Jahre
  • Woineshet Fikade
    • 200 $
    • 4 Jahre
  • Tigest Befirdu
    • 200 $
    • 4 Jahre
Spenden

Organisator und Spendenbegünstigter

Meklit Yirdaw
Organisator
Beaverton, OR
Andualem Hailu
Spendenbegünstigte

Deine einfache, effektive und sichere Anlaufstelle für Hilfe

  • Einfach

    Schnell und einfach spenden

  • Effektiv

    Unterstütze Menschen und Zwecke, die dir am Herzen liegen

  • Sicher

    Deine Spende ist durch die Spendengarantie von GoFundMe geschützt