Main fundraiser photo

ለዘማሪ ቀሲስ ግርማ አዳነ ቀብር ማስፈፀሚያ-For Priest Girma Adane's Funeral

Donation protected
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች!

በቦስተን የደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የነበሩት ሊቀ መዘምራን ቀሲስ ግርማ አዳነ (ወልደ ሰማዕት) ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በድንገት አርፈዋል፤፤ ይህም በቦስትን እና አካባቢው ለምንገኝ ካህናት፤ የሰበካ ጉባኤ አባላት እና ምእመናን እጅግ አስደንጋጭ እና መሪር ሃዘን ነው፤፤

ሊቀ መዘምራን ቀሲስ ግርማ አዳነ ደብራችንን በቅዳሴ፤ ዝማሬ፤ ስብከት እና ትምህርት ያገለገሉ ሲሆን የ37 ዓመት ጎልማሳ፤ ባለትዳር እና የ 6 ወር ህፃን አባት ነበሩ፤፤ የደብራችን ሰበካ ጉባኤም አስከሬናቸውን ወደ ሃገር ቤት በክብር ለመሸኘት፤ የሃገር ቤት የቀብር ስነ ስርአት ማስፈፀሚያ ወጭዎችን ለማገዝ እና ቤተሰቦቹን በገንዘብ ለመደገፍ ይህንን ጎፈንድሚ ከፍቷል፤፤ ይህንን የጎፈንድሚ አካውንት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ይስሃቅ አለሙ እንዲያስተዳድሩት ከቀሲስ ግርማ ባለቤት ወ/ሮ ቤተልሄም በኩል ውክልና የተሰጣቸው መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን።

በመሆኑም ምእመናን የቻላችሁትን ሁሉ ድጋፍ እንድታደርጉ በትህትና ስንጠይቅ የተሰበሰበው ገንዘብም ሙሉ በሙሉ እላይ ለተጠቀሱት ጉዳዮች ማስፈፀሚያ ብቻ የሚውል መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን፤፤ እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ይህንን ጉዳይ እንዲያስተባብር የተመረጠውን ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ፀሃፊ በሚከተሉት አድራሻዎች ማግኘት ይችላሉ፤፤

  • ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ይስሃቅ አለሙ፥ የኮሚቴው ሰብሳቢ፡ ስ/ቁ 6174477310
  • አቶ ዮናታን ዘነበ ፥ የኮሚቴው ፀሃፊ፡ ስ/ቁ 9784306759


እግዚአብሔር የሊቀ መዘምራን ቀሲስ ግርማ አዳነን ነብስ ይማርልን ፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይስጥልን!


ስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!

ማሳሰብያ፡
  • የጎፈንድሚ ቲፑን ዜሮ ማድረግ ከፈለጉ Enter custom tip የሚለውን በመጫን Tip amount እሚለው ባዶ ቦታ ላይ ዜሮ ያስገቡ::
  • ድጋፈዎን በ ዜል/Zelle በኩል መክፈል ከፈለጉ በሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ይስሃቅ አለሙ፥ የኮሚቴው ሰብሳቢ ስ/ቁ 6174477310 መጠቀም ይችላሉ::

ከዘማሪ ቀሲስ ግርማ አዳነ መዝሙሮች መካከል፡

***

In the name of the Father, and the Son, and the Holy Spirit, One God, Amen!

Dear Children of God,

It is with great sorrow that we inform you of the sudden passing of our beloved Singer and Priest, Girma Adane (Wolde Semayat), from the Debre Salam Saint Michael Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Boston. He departed from us on July 23, 2024, at the age of 37. His unexpected loss has been a profound shock and a source of deep sorrow for all our priests, parish councils, and parishioners in the Boston area.

Singer and Priest Girma Adane served our church through his participation in liturgies, singing, sermons, and teachings. He leaves behind a wife and a 6-month-old baby. In light of this tragic event, our congregation has established a GoFundMe account to:
  • Honorably return his body to his home country, Ethiopia.
  • Cover funeral and burial service related expenses.
  • Provide financial support to his family in Ethiopia.
We kindly request your generous donations to help cover these expenses and support his family in Ethiopia during this difficult time. All funds raised will be used exclusively for the purposes mentioned above. In addition, we would like you know that Kesis Girma's wife, Bethelhem, has authorized Kesis Yishak Alemu, Chairman of the Committee, to manage the fundraiser on her behalf.

For additional information or if you have any questions, please contact the chairman or secretary of the committee coordinating and managing the efforts:
  • Kesis Yishak Alemu, Chairman of the Committee:"//6174477310"
  • Mr. Yonatan Zenebe, Secretary of the Committee:"//9784306759"

May God grant him eternal rest and provide comfort to his family.

Glory be to God, to His Virgin Mother, and to the Holy Cross, Amen!

NB
  • If you want to set the GoFundMe tip to zero, press "Enter custom tip" and enter 0 in the tip amount field.
  • To pay your support through Zelle, use Kesis Yishak Alemu's phone number 6174477310.

P.S. Below are some of Kesis Girma Adane’s songs:

Donations 

  • Mi Ha
    • $100
    • 8 mos
  • Yodit Imeru
    • $100
    • 8 mos
  • S B
    • $100
    • 8 mos
  • Yenenesh Groom
    • $50
    • 8 mos
  • Anonymous
    • $40
    • 8 mos

Organizer

Yishak Alemu Gesesse
Organizer
Chelsea, MA

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee