
Ye Tsadkane Mariam Mahber
ማቴዎስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤
²⁰ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
የፃድቃኔ ማሪያም ማህበርተኞች በሳክራሜንቶ የመካነ ስብሀት ቅድስት ስላሴ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሆኑ አባላት የተመሰረተ ማህበር ነው::የመካነ ስብሐት ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን እንደሚታውቀው በዘመናችን በተከሰተው የኮቢድ 19 በሽታ ምክንያት ምዕመናን ከቤተ ክርስቲያን በመራቃቸው ቤተ ክርስቲያናችን የየዕለት አገልግሎት ለማከናወንና ያሉብንን ወጭዎች ለመሸፈን የአቅም መዳከም አጋጥሞናል ስለሆነም በቤተ ክርስቲያናችን አባላት የተመሰረተው በኅ አድራጊ የጻድቃኔ ማርያም ማህበርተኞች የስላሴን ቤተ ክርስቲያን ለመርዳት ከዚህ መዓት ያወጣንን የአለሙን ፈጣሪ እና ገዥ የሆነውን የመካነ ስብሐት ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ለመርዳት ሲሆን የማህበሩ አላማም በዋናነት የቤተክርስቲያኗን አገልግሎት ለማጠናከር ነው::
ስልሆነም ለሚያደርጉልን እገዛ እና ትብብር ሁሉ በእግዚአብሔርስም እናመሰግናለን::
እርዳታ በሚያደርጉበት ጊዜ (GoFundMe የሚጠይቅዎትን ተጨማሪ ችሮታ (ቲፕ) መክፈል አይኖርብዎትም። ተጨማሪ ችሮታው (ቲፕ) ወደ ፃድቃኔ ማሪያም ቻሪቲ አካውንት ገቢ አይሆንም። ስለዚህ ቲፕ ሳይጨምሩ እርዳታዎን ለመስጠት የሚከተለውን ያድርጉ፤ ‘በቲፑ ሳጥን ውስጥ ዜሮ (0.0) ከሞሉ በኋላ የእርዳታውን ገንዘብ በእርዳታው ቦታ ብቻ ይሙሉ::
የስላሴ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን
አሜን
Mathew 6
19 “Do not store up for yourselves treasures on earth, where moths and vermin destroy, and where thieves break in and steal. 20 But store up for yourselves treasures in heaven, where moths and vermin do not destroy, and where thieves do not break in and steal.
In the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, One God. Amen.
Ye Tsadkane Mariam Mahber is an association formed by members of Mekane Sebhat Kidist Selassie Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Sacramento, CA.
Because of the COVID-19 pandemic, our church service was interrupted for a while. As a result of the service interruption, the church experienced financial hardships and struggled to cover it's operating expenses. To help alleviate the hardships, YeTsadkane Mariam Mahber members created this gofundme account to raise funds to support the church with its monthly expenses as well as to ensure that church service will continue without interruption.
Thank you in advance for your support to the church. When you make donation,
you do not have to add tip since the tip does not benefit the church. Simply enter $0.00 in the entry for tip and only enter the amount of your donation.
May the Holy Trinity bless you!
Amen.