Main fundraiser photo

Ethio 360 Media -Your Support to Satellite Payment

Donation protected
ኢትዮ 360 ሚዲያን ባቋቋምን ጥቂት ወራት ውስጥ ሕዝባዊ አጋርነታችሁን በማሳየት  ባደረጋችሁልን ከፍተኛ የገንዘብና የምክር ድጋፍ በርካታ ወጭን የጠየቀ ዘመናዊ ስቱዲዮ ለመገንባት በቅተናል። በመርሕ እና በትክክለኛነት ላይ የተመሰረተ ሚዲያ አቋቁመን የኢትዮጵያዊያን እውነተኛ ድምጽ ለመሆን በገባነው ቃል መሰረትም በኑሮአችንን እና በሕይወታችን ዋጋ እየከፈልን  የሚገጥሙንን ፈተናዎች በማለፍ የእለት እለት መረጃዎችን ለሕዝባችን እያደረስን እንገኛለን።
ይሕም ሆኖ ግን በአሁኑ ጊዜ በፌስቡክና በዩቲዩብ የምናሰራጨው መረጃ በኢንተርኔት ዋጋ ውድነት ምክንያት በሀገር ወስጥ ላሉ ኢትዮጵያዊያን  ወገኖቻችን  እየደረሰ አለመሆኑን ተረድተናል።ይሕም የሆነው ባለን የአቅም ውስንነት ምክንያት ሳታላይት ላይ በፍጥነት ለመውጣት ባለመቻላችን እንደሆነ እንገነዘባለን። ስለሆነም ይሕንኑ ችግር ለመፍታት በቅርቡ በሳታላይት ላይ ፈጥነን ለመውጣትና የጀመርነውን ጥረት እውን ለማድረግ  የገቢ ማሰባሰቢያ መድረኮች እያዘጋጀን  እንገኛለን።
በመሆኑም ሰሞኑን የምናካሂደውን  የኢትዮ 360 ሚዲያ የስቱዲዮ ምረቃ መነሻ በማድረግ ዘላቂነት ያለውና ያልተቋረጠ የሳታላይት ስርጭት ለመጀመር ይህን የጎ ፈንድ ሚ የድጋፍ ጥሪ ለማቅረብ አስፈልጎናል። 
ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሀኒቱ እንዲሉ  በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን አንዣቦ የሚገኘውን ሀገራዊ  ችግር በጋራ ሆነን ለማስቀረትና  ሕዝብ ወሳኝ የሚሆንበትን እወነተኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመስረት ሕዝቡ በቂና እውነተኛ መረጃ እንዲያገኝ ሁላችሁም የአቅማችሁን እና የበኩላችሁን የገንዘብ  ድጋፍ  እንድታደርጉ የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን።ለምታደርጉት ድጋፍም ከወዲሁ እናመስግናለን።

የኢትዮ 360 ሚዲያ የስራ አመራር አባላት

Organizer

Liyou Tsegaye
Organizer
Annandale, VA

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee