Main fundraiser photo

Support Zerfie To Release Her CD

Donation protected
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
 
ዘማሪት ዘርፌ ከበደ  በቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን ሁሉ የምትወደድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ናት። በተለይ መንፈስ ቅዱስ በሚለው አልቨምዋ ብዙዎች ያውቁአታል።  ጥልቅ ትርጉም ባላቸውና የሰውን ልብ እየነኩ  ወደ እግዚአብሔር በሚያስጠጉ ዝማሬዎችዋ ብዙ ምእመናን ታንጸዋል ተገልግለዋል። ዘማሪት ዘርፌ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም ዙሪያ ሁሉ በሚኖሩ አብያተ ክርስቲያናት እየተጋበዘች በውጭው ዓለም ያለውንም ህዝባችንን እያገለገለች የምትገኝ ትጉ አገልጋይ ናት።

ዝማሬዎችዋን በሲዲ ከለቀቀች ወደ አራት ዓመት አካባቢ መሆኑን ስንረዳ ለምን ይህን ያህል ጊዜ ሌላ  የዝማሬ ሲዲ ሳትለቅ እንደዘገየች ጠየቅናት። መልስዋም የሲዲ ህትመት ሥራ ዋጋው እየጨመረ ከመሄዱና ለቀረጻና ለህትመት ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቅ መሆኑን ነገረችን።  ፥ በመሆኑም አለች ዘማሪት ዘርፌ በመሆኑም እግዚአብሔር ፈቅዶ ሲዲ ማሳተም እስከምችል ድረስ በተቻለኝ መጠን በዓለም ዙሪያ ሁሉ በአካል እየዞርኩ የምወደውን የእግዚአብሔርን ህዝብ እያገለገልኩ ነው አለችን። ሻማ ለራሱ እየቀለጠ ለሌሎቹ እንደሚያበራ ብዙ የቤተ ክርስቲያናችን አገልጋዮችም ለኛ እያበሩ ለራሳቸው ግን በብዙ ውጣ ውረድ እንደሚያልፉ ለሁላችንም ግልጽ ነው።

እኛም ይህንን ከሰማን በኋላ እንደ ጠራ ውሀ ኩልል እያሉ በመንፈሳዊ ጥም ያሉትን ብዙ ምእመናን ልብ የሚያረሰርሱትን ዝማሬዎችዋን በጊዜው ለህዝብ ጆሮ እንዳታደርስ ያገዳት የህትመት ወጪ መናር ከሆነ በዝማሬዎችዋ የተገለገልንና እየታንጽን ያለን እኛ ለምን ከጎንዋ ቆመን የድርሻችንን አንወጣም? ብለን አሰብንና ይህንን አካውንት ከፈትን። በመሆኑም በዝማሬዎችዋ የታነጻችሁ ምእመናን ሁሉ በቅርቡ ልትለቀው ያለውን ሲዲ ህትመት ለመደገፍ በሚቻላችሁ መጠን ከጎንዋ እንድትቆሙ በአክብሮት እንጋብዛችኋለን።   

እስከ ዛሬ ዝማሬዎችዋን እየሰማን ለተጠቀምንበት አገልግሎትዋ ያለንን አክብሮትና ፍቅር ይህን አጋጣሚ በመጠቀም እንግለጽላት።  አባቶቻችን ሲናገሩ «ሐምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ለሐምሳ ሰው ግን ጌጥ ነው» እንደሚሉት ሁላችን ከእህታችን ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ጎን ብንቆምና ድርሻችንን ብንወጣ በቅርቡ አዳዲስ ዝማሬዎችዋን እንሰማለን ብዙዎችም ይጠቀማሉ። ከዘማሪት ዘርፌ ጎን ስለቆማችሁና በሁሉም ስለምትደግፋዋት እርስዋን ወክለን እግዚአብሔር ይስጥልን እንላለን።

ZERFIE KEBEDE is an Ethiopian Orthodox Gospel singer. She is known by her amazing voice of Gospel song among all Ethiopians all around the world.

She released her first album entitled Ruhama, in 2009, which quickly became a success.

Zerfie again released her second album entitled Menfes Qedus (Holy Spirit) in 2013.

Now after four years she is ready to release her third album but as you all know the rising cost of studio and printing is holding her back from releasing her album on time.

Since she is serving us, the people of God we want to stand with and support her so that she can release her third album as quick as possible.

We encourage all her friends to take this opportunity to stand with Zerfie and support the release her album.  

Thank you for your support.

Organizer and beneficiary

Tsega S
Organizer
Rosharon, TX
ZERFIE KASSA
Beneficiary

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee