Foto principale della raccolta fondi

Save AbetirW & Help Displaced Amara

Donazione protetta

      አበጥር ወርቁ የ14 ዓመት ታዳጊ ነው። እስከ ቅርብ ጋዜ እንደማንኛውም ታዳጊ ብሩህ ተስፋ ነበረው። አበጥር ተወልዶ ባደገበት መተከል (የአሁኑ "ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል") በጉሙዝ ብሄረሰብ ተወላጆች አማራ ስለሆነ ብቻ ለህሊና በሚዘገንን መልኩ ብልቱ ተሰልቦ፣ አይኑ ተጎልጉሎ፣ ፊቱና አካሉ በስለት ተተልትሎ በሞትና በህይዎት መካከል ሆኖ ተስፋው እስከ ወዲያኛው እንዳይጨልም እየታገለ ይገኛል።

     የዚህ ታዳጊ ዘግናኝ ጉዳት በበርካታ አማራ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ግፍ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። በአሁኑ ወቅት በርካታ የአማራ ተወላጆች ያለ ምንም ምክንያት ተወልደው ካደጉበት ቀየ "መጤ" ተብለው ንብረታቸውን እየተዘረፉ እየተሰደዱ ሲሆን  እሚደርስላቸው ወገን፣ አቤት እሚልላቸው አካል ይፈልጋሉ።

     አበጥር በአሁኑ ሰዓት በባህዳር ህክምና እየተደረገለት ሲገኝ፣ ከተለያዪ “ክልሎች” “መጤ” ተብለው የተሰደዱ የአማራ ተወላጆች ደግሞ ገሚሶቹ በቤተ ክርስቲያን ገሚሶቹ ደግሞ መጠጊያ አጥተው ጎዳና ላይ ወድቀዋል።

     ይህ ግፍ እንዲቆም አማራና የአማራ ወዳጅ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲጮሁላቸው፣ በፀሎታቸው እንዲያስቧቸው፣ በተቻላቸው አቅም ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው አምባ የአማራ ባለሞያዎች ማህበር አበክሮ ይጠይቃል።

    አምባ የሚሰበሰበውን ገንዘብ አበጥርንና ቤተሰቦቹን ለመርዳት እና በግፍ "መጤ" ተብለው ከትውልድ ቦታቸው የተፈናቀሉ አማሮችን ለማቋቋሚያ ያውላል።


እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!


አምባ የአማራ ባለሞያዎች ማህበር

Organizzatore

Muluneh Abebe Yimer
Organizzatore
Leawood, KS

Il luogo in cui puoi aiutare in modo facile, efficace e affidabile

  • È facile

    Fai una donazione in modo facile e veloce

  • Efficace

    Offri un aiuto diretto per le persone e le cause che ti stanno a cuore

  • Affidabile

    La tua donazione è protetta dalla Garanzia GoFundMe Giving