አማራን እንደ ህዝብ ኢትዮጵያን እንደ ሃገር የማስቀጠል/የማዳን እና ለወገን ደጀን የመሆን ጥሪ!
አማራው በዜግነቱ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሚኖርባቸው የአገሪቱ ማዕዘናት በፖለቲካዊ እቅድ ተለይቶ ሲገደል፣ ሲፈናቀልና ሲሳደድ ለከፋ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተዳርጎ በችግር ሲማቅቅ በርካታ ዐሠርት አመታትን አሳልፏል። ይህ አንሶት ዛሬ "የለውጥ ዘመን" በሚባለው ጊዜ ከነዘር ምንዝሩ እየተጨፈጨፈ፣ የተገኘባቸው ቀዬዎችና ከተሞች እየወደሙ፣ በነፍስ የተረፈው በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ በአገሩ ስደተኛ ሆኖ አለበቂ መጠለያ የእለት ጉርስ ተመጽዋች ሆኖ ይገኛል።
ይባስ ብሎ ትህነግ "ከአማራ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ" ብሎ በከፈተብን ጦርነት እነሆ አገር መጋቢው የአማራ ገበሬ ማሳ በማለስለሻውና በመዝሪያው ወቅት፣ በሐምሌ፣ ትህነግ ጦርነት በከፈተባቸው ግንባሮች ሁሉ ህልውናውን ለማስከበር በመዋደቅ ላይ ይገኛል ። ይህ ጦርነት የአማራው ብቻ ሳይሆን የመላ አገሪቱ የህልውና ስጋት ነው። ይህን በችግር ኖሮ አገር ደግፎ ያኖረ ህዝብ በዚህ ክፉ ቀን መደገፍ ኢትዮጵያን ማዳን መሆኑን ማንም አገሩን የሚወድ አይስተውም። በዚህ እምነት በአሜሪካ፤ በካናዳ፤ በአውሮፓ በአውስትራሊያ ፤ ኒውዚ ላንድ እንዲሁም አፍሪካ እና እስያ ያሉ የአማራ ማህበራት ከወንፈል ጋር በመተባበር ለወገናችን የምግብ እና የህክምና እርዳታ የሚውል የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር አዘጋጅተናል።
በዚህም ሆነ በሌሎች ተመሳሳይ የእርዳታ ማሰባሰቢያ አጋርነታችሁን ላሳያችሁ እርዳታው በታቀደለት ወገናችን ስም ከፍ ያለ ምስጋና ይድረሳችሁ። የመርሀ ግብሩን ሂደት በየጊዜው በኢሜይልና በዚህ ገጽ እናሳውቃለን።
ከዚህ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ውጭ የሚደረጉ እንደ ቴሌቶን ያሉ መርሐ ግብሮች እያዘጋጀን እናስ ታውቃለን።
የሚከተሉትን አማራጭ የገንዘብ መለገሻ መንገዶች ሊጠቀሙ ይችላሉ:: Please include “Amhara Emergency Fund” in the comment section
1. Wonfel Paypal Giving Acct: paypal.com/us/fundraiser/charity/3558428
2. For Venmo and Zelle please use the Wonfel email: info'@‘wonfel.org
*************
For the last three years, Amharas were under consistent attack and people have been suffering. Millions have been displaced, thousands wounded and hundreds of children orphaned. The current conflict in northern Ethiopia is worsening the situation specifically after TPLF declared an all out war on Amhara. It is high time for us Ethiopians to stand together and look after one another. Let’s act collectively and contain our brothers and sisters’ suffering before it spreads to the rest of our country.
Your donations will go a great length to provide emergency food, medical supplies and shelter.
If not NOW, when? If not US, who will stand for our people?
**********************
Partcipating Organizations
Federation of Amharas in North America (FANA)
Amhara Association of America - [email redacted]
Amhara Professionals Union - [email redacted]
Amhara Association of Colorado - [email redacted]
Amhara People’s Civic Organization (Dallas) - [email redacted]
Amhara Association in Georgia - [email redacted]
Amhara Association in Seattle - [email redacted]
Amhara Association of California - [email redacted]
Amhara Association of Los Angeles - [email redacted]
Amhara Association of Nevada - [email redacted]
Amhara Heritage Society of Minnesota - [email redacted]
Canadian Amhara Societies Alliance (CASA) – [email redacted]
International Amhara Alliance (IAA) – [email redacted]
Amhara Support, Relief & Rehabilitation Association (ASRRA) - New Zealand – [email redacted]
Yotor Farmers' Association [email redacted]
International Amhara Union [email redacted]
Amhara Association of Norway
Wonfel Aid [email redacted]
Interviews
https://youtu.be/U6KrypquaDo
https://youtu.be/Osqu1MBH9MY
https://youtu.be/5gZE3PnFqd0
https://youtu.be/LTILl-HTZzw
https://youtu.be/qYDOtU_2dq8
https://youtu.be/Tx29iBwQeaA
https://youtu.be/U6KrypquaDo
https://youtu.be/jCzv9G6uDbU
https://youtu.be/S5O6K9q6guY